Fana: At a Speed of Life!

በአሜሪካ ካሮላይና ግዛት በተከሰተ ዝናብ የቀላቀለ አውሎ ነፋስ 30 ሰዎች ሞቱ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ ሰሜናዊ ካሮላይና ግዛት በተከሰተ ዝናብ የቀላቀለ ከባድ አውሎ ነፋስ አደጋ 30 ሰዎች መሞታቸው ተገለፀ፡፡

አደጋው በፍሎሪዳ መከሰቱ የተገለፀ ሲሆን የጆርጂያ ግዛትን አቋርጦ በመተላለፍ በካሮላይና  የተለያዩ ከተሞች ጉዳት ማድረሱ ተነግሯል።

የድንገተኛ አደጋ ባለሥልጣን የሆኑት ራያን ኮል÷ በካሮላይና ግዛት በምትገኘው አሽቪል ከተማ የተከሰተው ከባድ አውሎ ነፋስ ከፍተኛ ውድመት ማድረሱን ተናግረዋል፡፡

አደጋው ባለፈው ሀሙስ በፍሎሪዳ በተከሰተበት ወቅትም 105 ሰዎችን ለህልፈተ ህይወት መዳረጉ ተገልጿል።

በርካታ መኖሪያ ቤቶችን ባወደመው በዚህ ከባድ አደጋው ከ1 ሺህ በላይ ሰዎች ያሉበት እንዳልታወቀ ተገልጿል፡፡

የአሜሪካ ቀይ መስቀል በአደጋው የተጎዱ ወገኖችን በጊዜያዊነት ለማቋቋም ከ140 መጠለያ ስፍራዎችን ማዘጋጀቱ የተገለፀ ሲሆን፤ እስካሁን ከ2 ሺህ በላይ አሜሪካውያን ዜጎች በጊዜያዊ መጠለያ ስፍራዎች ይገኛሉ ተብሏል፡፡

አደጋውን ተከትሎ የነፍስ አድን ስራዎችን ለማከናወን እና አደጋውን ለመከላከል በአጠቃላይ በስድስት ግዛቶች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.