Fana: At a Speed of Life!

የትግራይ ሕዝብ ከመቼውም ጊዜ በላይ ሰላሙን እንዲጠብቅ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የተጀመሩ የልማት ሥራዎች ከፍጻሜ እንዲደርሱ ሕዝቡ ከመቼውም ጊዜ በላይ ሰላሙን እንዲጠብቅ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መሥተዳድር ጌታቸው ረዳ ጥሪ አቀረቡ፡፡

ርዕሰ መሥተዳድሩ በትግራይ ደቡብ ምሥራቅ ዞን በሕዝብ ከተወከሉ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጋር በወቅታዊ ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡

በዚሁ ወቅትም የውይይቱ ዋና ዓላማ “በክልሉ የተጀመሩ ሥራዎች እንዴት ማጠናቀቅ እንዳለብን በመነጋገር የመፍትሄ ሐሳቦችን ለማስቀመጥ ነው” ብለዋል፡፡

የትግራይ ሕዝብ አሁን ላይ ከመቼውም ጊዜ በላይ ሰላምና አንድነት ያስፈልገዋል ያሉት አቶ ጌታቸው፥ በዚህም የክልሉ ሕዝብ የልማት ተግባራቱን እያከናወነ ሰላሙንና አንድነቱን መጠበቅ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

ሕዝቡ የጀመራቸውን የልማት ሥራዎች ከዳር ለማድረስም ይጠበቅበታል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.