Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ታዬ ከብሪታኒያ የባለብዙ ወገን ግንኙነት ጉዳዮች፣ ሰብዓዊ መብቶችና የአፍሪካ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከብሪታኒያ የባለብዙ ወገን ግንኙነት ጉዳዮች፣ ሰብዓዊ መብቶች እና የአፍሪካ ጉዳይ ሚኒስትር ሎርድ ኮሊንስ ጋር ተወያይተዋል።

ውይይቱ የተደረገው ከ79ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ጠቅላላ ጉባዔ ጎን ለጎን መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

አምባሳደር ታዬ በውይይታቸው ላይ በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ ሁኔታ እና ኢትዮጵያ በቀጣናው ሰላም፣ ልማት እና የኢኮኖሚ ትስስር እንዲፈጠር እያደረገችው ያለውን ጥረት አስረድተዋል፡፡

ሎርድ ኮሊንስ በበኩላቸው በቀጣናው የኢኮኖሚ ትስስር እንዲፈጠር ለማድረግ ዋና አንቀሳቃሽ በሆነው የኢኮኖሚ ልማት ላይ ማተኮር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ሁለቱ አካላት በቀጣናው ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ መሥራት እንዲሁም ንግድ እና ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ በማድረግ ጉልህ አበርክቶ እንዳላቸው የተነሳ ሲሆን÷ በቀጣይም ተመሳሳይ ውይይት ለማድረግ መስማማታቸው ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.