Fana: At a Speed of Life!

በኢሬቻ በዓል ላይ ለመሳተፍ ወደ ሀገር ቤት ለገቡ የዳያስፖራ አባላት አቀባበል እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል በኢሬቻ በዓል ላይ ለመሳተፍ ወደ ሀገር ቤት ለገቡ የዳያስፖራ አባላት አቀባበል እያደረገ ነው።

የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል ”ኢሬቻ ለባህላችን ሕዳሴ” በሚል መሪ ሃሳብ በመጪው ቅዳሜ መስከረም 25 በአዲስ አበባ ሆራ ፊንፊኔ እንዲሁም በቀጣዩ ቀን እሁድ መስከረም 26 ቀን 2017ዓ.ም ደግሞ በቢሾፍቱ ሆራ አርሰዴ እንደሚከበር ታውቋል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ባቀረቡት ጥሪ መሠረትም በርካታ የዳያስፖራ አባላት በበዓሉ ላይ ለመሳተፍ ወደ ሀገር ቤት እየገቡ ነው፡፡

ለእነዚህ ዳያስፖራዎችም የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት የአቀባበል መርሃ ግብር እያካሄደ እንደሚገኝ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.