Fana: At a Speed of Life!

መድሃኒት የተላመዱ ተህዋስያን የሚያስከትሉትን ጉዳት ለመቀነስ ትብብር እንደሚያስፈልግ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) መድሃኒት የተላመዱ ተህዋስያን የሚያስከትሉትን ጉዳት ለመቀነስ ዓለም አቀፍ ትብብር እንደሚጠይቅ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ገለጹ፡፡

ዶ/ር መቅደስ መድሃኒት የተላመዱ ተህዋስያን ላይ ለመምከር በተዘጋጀው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 79ኛው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ተሳትፈዋል፡፡

ሚኒስትሯ በዚህ ወቅት÷ ኢትዮጵያ መድሃኒት የተላመዱ ተህዋስያን የሚያስከትሉትን ጉዳት ለመቀነስ ትኩረት ሰጥታ እንደምትሰራ ገልጸዋል፡፡

መድሃኒት የተላመዱ ተህዋስያን የሚያስከትሉት ጉዳት ዓለም አቀፋዊ ስጋት መሆኑና ዓለም አቀፍ ትብብርን የሚጠይቅ መሆኑን ሚኒስትሯ አጽንኦት ሰጥተው መናገራቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.