Fana: At a Speed of Life!

ም/ቤቱ ሕገ-መንግስታዊ ተልዕኮዎችን በብቃት መወጣት የሚያስችሉ ተግባራትን እያከናወነ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሕገ-መንግስታዊ ተልዕኮዎችን በብቃት መወጣት የሚያስችሉ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የም/ቤቱ 4ኛ ዓመት የምርጫ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ቅድመ ዝግጅት ሥራዎች የጽ/ቤቱ አመራሮችና ዳይሬክተሮች በተገኙበት ተገምግመዋል፡፡

በግምገማው ም/ቤቱ በ4ኛ ዓመት የሥራ ዘመኑ በሕገ መንግስቱ የተጣሉበትን ተልዕኮዎች በብቃት መወጣት የሚያስችሉ የተለያዩ ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

የምክር ቤቱ ጽ/ቤት ዋና ጸሃፊ ምስራቅ መኮንን (ዶ/ር)÷ ም/ቤቱ በቀጣይ ሥራዎቹ ስኬታማ እንዲሆን የሚያስችሉ የተለያዩ ሥራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ አስረድተዋል፡፡

ሥራዎች በፍጥነትና በጥራት እንዲሰሩ አቅጣጫ መቀመጡንም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

ጽ/ቤቱ የተለያዩ ክፍተቶችን በማረም ብቃት ያለው የክትትልና ቁጥጥር ተግባር ማከናወን የሚያስችለውን ሙያዊ ድጋፍና አስተዳደራዊ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ መሆን እንዳለበትም ዋና ጸሃፊዋ አስገንዝበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.