Fana: At a Speed of Life!

የኮደርስ ስልጠና በተለያዩ ዘርፎች ተወዳዳሪ ለመሆን የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዝ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮደርስ ስልጠና ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ በኢኮኖሚ፣ በጸጥታና በቴክኖሎጂ የምታደርገውን ውድድር በብቃት እንድትወጣ ያግዛል ሲሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር እንዳሻው ጣሰው ገለጹ፡፡

የስልጠናው ዋና ዓላማ የዜጎችን የዲጂታል ክኅሎት በማዳበር ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነታቸውን ማሳደግ መሆኑን አቶ እንዳሻው ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት በሁሉም ዘርፎች ፈጣን እድገት ለማምጣት ዲጅታል ኢትዮጵያ 2025 እቅድ ነድፋ ለተግባራዊነቱ ርብርብ ስታደርግ መቆየቷን ለኢዜአ ገልጸዋል፡፡

በዚህ ዘርፍ ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ባከናወነቻቸው ተግባራት በርካታ ለውጦች መመዝገባቸውን አንስተዋል፡፡

በመተግበር ላይ ያለው ኮደርስ ኢንሼቲቭ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ደረጃ በኢኮኖሚ፣ በጸጥታና በቴክኖሎጂ ዘርፎች የመወዳደር አቅም ለማሳደግ እንደሚያግዝም ነው ያስረዱት፡፡

የኮደርስ ስልጠና የወጣቶችን ተወዳዳሪነት በማሳደግ ከጠባቂነት ወደ ስራ ፈጣሪነት እንዲሸጋገሩ የሚያግዝ መሆኑን ገልጸው÷ ይህን አጋጣሚ በመጠቀም ሁሉም በስልጠናው እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.