Fana: At a Speed of Life!

የኮደርስ ሥልጠና በቴክኖሎጂ ብቁ ትውልድ ለመፍጠር የሚያስችል ነው- አቶ ደስታ ሌዳሞ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮደርስ ሥልጠና በቴክኖሎጂ ብቁ ትውልድ በማፍራት ዘመኑን የዋጀ ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት ያስቻላል ሲሉ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ደስታ ሌዳሞ ገለፁ።

ስልጠናው በቴክኖሎጂ ብቁ ትውልድ ለመፍጠር የሚያስችል መሆኑን የገለጹት አቶ ደስታ÷ ዜጎች በሀገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የሥራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑም ያግዛል ብለዋል፡፡

የዜጎችን የቴክኖሎጂ አጠቃቀም በማጎልበት የኢትዮጵያን የዲጂታል ጉዞ በማፋጠን ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት ለመስጠት ዕድል እንደሚፍጥርም ነው ለኢዜአ የተናገሩት፡፡

ዜጎች ይህንን ጠቃሚ የሆነ ስልጠና በመውሰድ ራሳቸውን፣ ሀገራቸውና ሕዝባቸውን እንዲጠቅሙ ጥሪ አቅርበዋል።

የኮደርስ ስልጠና በቀጣዮቹ ሶስት ዓመታት 5 ሚሊየን ዜጎችን በዌብ ፕሮግራሚንግ፣ በአንድሮይድ ማበልፀግ፣ ዳታ ሳይንስና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መሠረታዊ የዲጂታል ክኅሎት እንዲኖራቸው የሚያደርግ ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.