Fana: At a Speed of Life!

የመስቀል ደመራ በዓል በተለያዩ ክልሎች እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስቀል ደመራ በዓል የተለያዩ ክልሎች በመከበር ላይ ይገኛል፡፡

በዓሉ በጋምቤላ ከተማ በርካታ ምዕምናን በተገኙበት በድምቀት እየተከበረ ሲሆን በአከባበር ስነ ስርዓቱ የዕምነቱ አባቶች፣ ምዕመናንና የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች መታደማቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያሳያል፡፡

በተመሳሳይ በዓሉ በድሬዳዋ አስተዳደር የሀይማኖት አባቶች እና በርካታ የእምነቱ ተከታዮች በተገኙበት በምድር ባቡር አደባባይ በተለያዩ ሀይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶች በድምቀት እየተከበረ እንደሚገኝ የከተማው ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል።

እንዲሁም በዓሉ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ በተለያዩ ኃይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶች እየተከበረ ሲሆን የሃይማኖት አባቶች፣ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎችና የእምነቱ ተከታዮች መገኘታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በዓሉ በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማም የሃይማኖት አባቶች፣ የክልሉ የስራ ኃላፊዎች፣ የእምነቱ ተከታዮችና ሌሎች የበዓሉ ታዳሚዎች በተገኙበት በድምቀት እየተከበረ እንደሚገኝ የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.