የ2024 የአፍሪካ የጠረጴዛ ቴኒስ ሻምፒዮና በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ይካሄዳል
አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2024 የአፍሪካ የጠረጴዛ ቴኒስ ሻምፒዮና በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት የፊታችን ጥቅምት ወር ላይ ይካሄዳል፡፡
ከጥቅምት 2 እስከ 9 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ በሚካሄደው ሻምፒዮና ላይ ከ300 በላይ ስፖርተኞችና ተጋባዥ እንግዶች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል ተብሏል፡፡
በውድድሩ የሚያሸንፉ ስፖርተኞች የ25 ሺህ ዶላር ተሸላሚ እንደሚ ይሆናሉ መባሉን የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡
ከመስከረም 29 እስከ ጥቅምት 2 ውድድሩ የሚመራበት ስልጠና እና ጥቅምት 5 ደግሞ የአፍሪካ ጠረጴዛ ቴኒስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባዔ እንደሚካሄድም ተገልጿል፡፡