Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ከ8 ሚሊየን ኩንታል በላይ የሩዝ ምርት ይጠበቃል ተባለ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በዘንድሮው የምርት ዘመን በሩዝ ሰብል ከለማው መሬት ከስምንት ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠበቅ የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።

በቢሮው የሩዝ ሰብል ልማት አስተባባሪ ወይዘሮ እንየ አሰፋ እንደገለጹት÷ በምርት ዘመኑ 150 ሺህ 226 ሄክታር መሬት በሩዝ ሰብል ለምቷል።

በማዕከላዊ፣ ምዕራብና ደቡብ ጎንደር፣ በአዊና ሰሜን ጎጃም ዞኖች የሩዝ ልማቱ መካሄዱን ጠቅሰው÷ አጠቃላይ በሩዝ ከለማው መሬት ከ107 ሺህ ሄክታር የሚበልጠው በኩታ ገጠም የለማ መሆኑን ተናግረዋል።

በምርት ዘመኑ በሩዝ ከለማው መሬት ከስምንት ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ መታቀዱ መገለፁን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በቀጣይም ልማቱን በማስፋፋትና ምርታማነቱን በማሳደግ ከውጭ የሚገባውን የሩዝ ምርት በሀገር ውስጥ ለመተካት የተያዘው ግብ እንዲሳካ ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል ብለዋል።

በአማራ ክልል ባለፈው ዓመት በክልሉ በሩዝ ሰብል ከለማው ከ82 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ከ4 ነጥብ 1 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት መገኘቱም ተመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.