Fana: At a Speed of Life!

ማይንቴክስ የማዕድንና የቴክኖሎጂ ኤክስፖ በሕዳር ወር ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) 3ኛው ማይንቴክስ የማዕድንና የቴክኖሎጂ ኤክስፖ ከሕዳር 14 እስከ 17 ቀን 2017 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚካሄድ የማዕድን ሚኒስቴር አስታውቋል።

በኤክስፖው በርካታ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች እንደሚሳተፉና ለሁነቱ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉ ተገልጿል፡፡

ኤክስፖው ሀገር በቀል ድርጅቶች ምርታቸውን ለዓለም እንዲያስተዋውቁና እንዲሸጡ ምቹ እድል እንደሚፈጥር መጠቆሙንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።

በማዕድና በቴክኖሎጂ ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶች በኤክስፖው ላይ በመሳተፍ ምርትና አገልግሎታቸውን እንዲያስተዋውቁምጥሪ ቀርቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.