Fana: At a Speed of Life!

መሳላን ምክንያት በማድረግ የባህልና ጥናት ሲምፖዚየም እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የከንባታ ዘመን መለወጫ መሳላን ምክንያት በማድረግ የባህልና ጥናት ሲምፖዚየም እየተካሄደ ነው::

በሲምፖዚየሙ ‘መሳላና አንድነት’ በሚል ርዕስ ጥናታዊ ፅሁፍ ቀርቧል፡፡

ጥናታዊ ፅሁፉን ያቀረቡት ተከተል ዮሃንስ (ፕ/ር)፤ የአንድነት ትርጉም በሚያግባቡ ጉዳዮች ላይ መግባባት እንዲሁም በማያግባቡ ጉዳዮች ላይ ደግሞ ልዩነትን አክብሮ ለሀገር እድገት መስራት ነው ብለዋል።

ዓድዋን በአንድነት ስናሸንፍ ልዩነቶች በፖለቲከኞች መካከል ሳይኖር ቀርቶ ሳይሆን የትኛውም ልዩነት በሀገር ጉዳይ እንዳማያራርቅ በግልፅ ያሳየ አኩሪ ታሪክ ነው ሲሉም ተናግረዋል።

አባይን የፈጠሩት እንደ ሰከላ ያሉ ትናንሽ ጅረቶች መሆናቸውን ጠቅሰው፤ እኛም ትናንሽ የተባለውን ሀብታችንን አሰባስበን ከሰራን የሚታየው የልማት ጥያቄ ያለ ማንም ድጋፍ ሊሳካ ይችላል ብለዋል።

እውነትና ፍቅርን መሰረት ያደረገ አንድነት ሀገርን እንደሚያሻግር አስገንዝበው፤ በአንዱ ጉዳት መሻገርን በመጣል በአንድነት በመፅናት ሀገርን ለማሻገር መስራት እንደሚገባ አስረድተዋል።

በጥላሁን ይልማና ጀማል ከዲሮ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.