Fana: At a Speed of Life!

በቅርቡ የተገነቡ የቱሪዝም ሀብቶች ኢትዮጵያ ያላትን አስውባ ጥቅም ላይ እንድታውል ዕድል ሰጥቷል ተባለ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግሥት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአዲስ አበባና ክልሎች የገነባቸው የቱሪዝም ሀብቶች ኢትዮጵያ ያላትን አስውባ ጥቅም ላይ እንድታውል ዕድል መስጠቱን የተለያዩ አስጎብኝ ድርጅቶች ገለጹ፡፡

ጎብኝዎች ለቀናት በቂ እረፍት አግኝተው የሚመለሱባቸው የመዝናኛ ሥፍራዎች በስፋትና በጥራት እየተገነቡ መሆኑንም ነው የድርጅቶቹ የሥራ ኃላፊዎች የገለጹት፡፡

የኢትዮጵያ መልክዓ-ምድራዊ አቀማመጥ፣ የዓየር ሁኔታና ምቹ መስተንግዶ ቱሪስቶችን የመሳብ አቅም እንዳላቸው ጠቅሰው÷ እነዚህ እምቅ የቱሪዝም ሃብቶች የሀገርን ገጽታ ከመገንባት ባሻገር የኢኮኖሚ መሰረት መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

መንግሥት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአዲስ አበባና ክልሎች የሚገነባቸው የቱሪዝም ሀብቶች ኢትዮጵያ ያላትን አሳምራና አስውባ ጥቅም ላይ እንድታውል ዕድል የሚሰጥ መሆኑንም ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

በጎርጎራ፣ ወንጭ፣ በአዲስ አበባና ሌሎችም አካባቢዎች የተገነቡ የቱሪዝም መስኅብ ስፍራዎች ለሀገር ሃብትና ለበርካቶችም የሥራ መፍጠራቸውን ጠቁመዋል፡፡

በቱሪዝም ኢንቨስትመንት ለሚሰማሩ አልሚዎች በምን አይነት የጥራት ደረጃ መሥራት እንዳለባቸውም በጥሩ ተሞክሮነት የሚወሰዱ ናቸው ብለዋል፡፡

ባለፉት የለውጥ ዓመታት ብዙ አዳዲስ የቱሪዝም ሀብቶች ለምተዋል፤ ነባሮችም ታድሰዋል ያሉ የሥራ ኃላፊዎቹ÷ ይህም በዘርፉ የተሰማሩ አስጎብኝ ድርጅቶችን ያነቃቃና የቱሪስት ፍሰቱንም እየጨመረ መምጣቱን አንስተዋል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.