Fana: At a Speed of Life!

የጎቤና ሽኖየ ማጠቃለያ መርሐ-ግብር በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የጎቤና ሽኖየ ማጠቃለያ መርሐ-ግብር በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡

በኦሮሞ ሕዝብ ባህል በጳጉሜን ወር ለአዲስ ዓመት አቀባበል ሴቶች ሽኖየ ወንዶች ደግሞ የጎቤ ጨዋታ ከመሥከረም ጀምሮ ይጫወታሉ።

በዚህ መሠረትት ከጳጉሜን 2016 ጀምሮ ወጣቶች እንኳን አደረሣችሁ ጨዋታ በአዲስ አበባ እና በሸገር ከተማ አስተዳደር አካሂደዋል።

በዋነኝነትም በጎዳና፣ በአደባባይ በታዋቂ ግለሰቦች መኖሪያ ቤት፣ በከፍተኛ አመራሮች መኖሪያ ቤትና በተቋማት እንዲሁም በመሰል ሥፍራዎች የእንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞት እና የተለያዩ ስጦታዎችን ሲቀበሉ ቆይተዋል።

በዛሬው ዕለትም በአዲስ አበባና በሸገር ከተማ አስተዳደር ሲካሄድ የቆየው የጎቤና ሽኖየ ጨዋታ በአባቶች ምርቃት እንደሚጠናቀቅ የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.