Fana: At a Speed of Life!

ወላይታ ድቻ ኢትዮ ኤሌክትሪክን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሣምንት ጨዋታ ወላይታ ድቻ ኢትዮ ኤሌክትሪክን 3 ለ 2 አሸነፈ።

ቀን 10 ሰዓት ላይ በድሬዳዋ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ወላይታ ድቻ ኢትዮ ኤሌክትሪክን ጌታሁን ባፋ (በራስ ላይ)፣ ተስፋዬ መላኩ እና ካርሎስ ዳምጠው ባስቆጠሯቸው ግቦች ድል አድርጓል።

በዚህም በሊጉ የመጀመሪያ ጨዋታው ሶስት ነጥብ ይዞ ወጥቷል።

ኢትዮ ኤሌክትሪክ እዮብ ገብረማሪያም እና አቤል ሀብታሙ አማካኝነት ሁለት ጎሎች አስቆጥረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.