Fana: At a Speed of Life!

መቻል ስፖርት ክለብን ወደ ቀደመ ክብሩ ለመመለስ እየተሠራ መሆኑ ተነገረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የመቻል ስፖርት ክለብን ወደ ከፍታው ለመመለስ እየተሰራ መሆኑን የመከላከያ ሠራዊት የሥነ ልቦና ግንባታ ዋና ዳይሬክተር ሜጄር ጄኔራል እንዳልካቸው ወልደኪዳን ተናግረዋል።

የክለቡን ታሪክ በመፈተሽ የቦርድ አመራር በማደራጀትና አቅጣጫ በመሥጠት ወደ ሥራ እንዲገባ በማድረግ ሠፊ ሥራ ተሠርቷል ብለዋል።

እንደ ፖርቹጋላዊው ሉዊስ ናኒ አይነት ታዋቂ የውጭ ተጫዋቾችን በመጋበዝ ተሞክሯቸውን እንዲያስተላልፉ ማድረግ ከተሰሩ ስራዎች መካከል እንደሚጠቀስም አንስተዋል።

በዓመቱ የማጠቃለያ መርሃ ግብር በውድድር ዓመቱ የተገኙ ዋንጫዎችን የማሥረከብ መርሃ ግብር የተካሄደ ሲሆን፤ በሁሉም ደረጃ ለሚገኘው የእግር ኳስ ቡድን 6 ሚሊየን 17 ሺህ ብር፤ ለአትሌቲክስ ቡድኑ ደግሞ 1 ሚሊየን 737 ሺህ 200 ብር የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.