Fana: At a Speed of Life!

ምስራቅ ዕዝ ማንኛውንም ተልዕኮ መወጣት የሚያስችል የዝግጁነት ደረጃ ላይ ይገኛል – ሌ/ጀ መሃመድ ተሰማ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 206 (ኤፍ ቢ ሲ) ምስራቅ ዕዝ ማንኛውንም ተልዕኮ መወጣት የሚያስችል የዝግጁነት ደረጃ ላይ ይገኛል ሲሉ የዕዙ አዛዥ ሌተናል ጀኔራል መሃመድ ተሰማ ገለጹ፡፡

ሌ/ጀ መሃመድ ተሰማ እንዳሉት÷ ዕዙ ከባድ ሀገራዊ ግዳጆችን በአስተማማኝ መልኩ መወጣት የሚችልበት ወታደራዊና ሥነ-ልቦናዊ የዝግጁነት ደረጃው በላቀ የመፈፀም ብቃት ላይ ይገኛል፡፡

ዕዙ በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ተሰማርቶ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ግዳጆችን በአስተማማኝ መልኩ መወጣት የሚያስችል ወታደራዊና ሥነ-ልቦናዊ ዝግጁነት ላይ እንደሚገኝም አረጋግጠዋል፡፡

ነባርና ረጅም ዕድሜ ያለው አንጋፋው የምስራቅ ዕዝ÷ የሚሰጠውን ማንኛውንም ግዳጅ በድል አድራጊነት የሚደመድም እንዲሆን የቀጣናውን የጸጥታ ሁኔታ ያገናዘቡ ተግባራትን ማከናወን እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በኢትዮጵያ የሚከሰቱ ጦርነቶችን በሚገባ እየመከትን በአሸናፊነት ከማጠናቀቃችን ባሻገር ሰራዊታችን በተሰማራበት ጎረቤት ሀገር በፈፀማቸው ግዳጆች ኢትዮጵያዊያንን ያኮራ መሆኑን አውስተዋል፡፡

ሌተናል ጀነራሉ በቀጣይ የሰራዊቱን የማድረግ አቅም የበለጠ አጎልብተን መቀጠል አለብን ሲሉ ማስገንዘባቸውንም የመከላከያ ሰራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.