ለመቄዶኒያ የአረጋውያን እና የአዕምሮ ህሙማን ማዕከል 9 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ዋጋ ያለው ድጋፍ ተደረገ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ ለመቄዶኒያ የአረጋውያን እና የአዕምሮ ህሙማን ማዕከል 9 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ዋጋ ያለው ድጋፍ አድርገዋል፡፡
ድጋፉም በዓይነት ከ7 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ መሆኑን እና ለ7 ሺህ 500 አረጋውያን በ 1 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር ማዕድ ማጋራትን ያካተተ መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ባስተላለፉት መልዕክት÷ በጎነትን በማስቀደም እና ሰብዓዊነትን በማጎልበት ግለሰቦች እና ተቋማት ማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡
የማዕከሉ መሥራች ቢኒያም በለጠ በበኩላቸው ተቋማቱ ላደረጉት ድጋፍ አመሥግነው÷ በርካታ አረጋውያንን መደገፍ እንዲቻል ግለሰቦችና ተቋማት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቀርበዋል፡፡