ካሳለፍናቸው ፈተናዎች በመማር መልካም ለማድረግ መስራት ይገባናል -አቶ ብናልፍ አንዷለም
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ካሳለፍናቸው ፈተናዎች በመማር አዲሱን ዓመት መልካም ለማድረግ መስራት ይገባናል ሲሉ የሰላም ሚኒስትሩ ብናልፍ አንዷለም ገለፁ፡፡
የሰላም ሚኒስቴር አመራሮች እና ሰራተኞች በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከበረ የሚገኘውን የኅብር ቀን ” ኅብር ለሰላም” በሚል መሪ ሃሳብ እያከበሩ ይገኛሉ።
በመርሐ ግብሩ የሰላም ሚኒስትሩ ብናልፍ አንዷለም÷ባለፈው ዓመት ብዙ ፈተና እና ዕድሎችን ያሳለፍንበት ዓመት ነበር ፤በፈተና ያሳለፍናቸውን ቀናትን በማየት መልካም የሆነ ዓመት ለማድረግ የምንሰራበት ጊዜ ነው ብለዋል፡፡
በመርሐግብርሩ ኅብረትንና አጋርነትን የሚያሳዩ ስጦታዎች ለተቋሙ ሰራተኞች እና ለሌሎች ግለሰቦች መበርከቱን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡