Fana: At a Speed of Life!

ሰዎችን ማክበርና መሸለም ሌሎች በጎ ሰዎችን ለማፍራት ይረዳል – ፕሬዚዳንት ሳኅለወርቅ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የላቀ አፈጻጸም ያላቸው ሰዎችን ማክበርና መሸለም ሌሎች በጎ ሰዎችን ለማፍራት ይረዳል ሲሉ ፕሬዚዳንት ሳኅለወርቅ ዘውዴ ገለጹ፡፡

የ2016 ዓ.ም 12ኛው ዙር የበጎ ሰው ሽልማት ሥነ-ሥርዓት በዛሬው ዕለት ተካሂዷል፡፡

በሽልማት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳኅለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ የተለያዩ እንግዶች ተገኝተዋል።

ፕሬዚዳንት ሳኅለወርቅ በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷ ከራሳቸው እና ከቤተሰቦቻቸው አልፈው ለሀገር የሚጠቅም ስራ ለሰሩ ሰዎች በሕይወት እያሉ የሚገባቸውን ክብር መስጠት ይገባል፡፡

የላቀ አስተዋጽኦ ለአበረከቱ የሀገር ባለውለታዎች እውቅና መስጠት የበለጠ እንዲሰሩ ያበረታታል፤ ሌሎች ሰዎችም መሰል ተግባራትን እንዲያከናውኑ በር ይከፍታል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በኢትዮጵያ በተለይ ሰዎች በሞት ከዚህ ዓለም ከመለየታቸው በፊት ለአበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና መስጠት መለመድ እና ማደግ እንዳለበትም አስገንዝበዋል፡፡

እንደዚህ አይነት ተግባር ሌሎች በጎ ሰዎችን በማፍራት ረገድ ጉልህ ድርሻ እንደሚያበረክት አስረድተዋል፡፡

የበጎ ሰው ሽልማት ድርጅት እያከናወነ ያለው ተግባር ይበል የሚባል እና ለሌሎችም ምሳሌ የሚሆን መሆኑን ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.