670 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 670 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ለተመላሾቹም ተገቢውን ድጋፍ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡
ከሚያዝያ 4 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ ባለው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ሥራ እስከ አሁን ከ77 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉም ነው የተገለጸው፡፡