Fana: At a Speed of Life!

በመስዋዕትነት የሀገርን ሉዓላዊነት መጠበቅ ከክብር በላይ ነው- አቶ አሻድሊ ሀሰን

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በውድ መስዋዕትነት የሀገርን ሉዓላዊነት መጠበቅ ከክብር ሁሉ የላቀ ነው ሲሉ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አሻድሊ ሀሰን አስገነዘቡ፡፡

በክልሉ ጳጉሜን 3 “የሉዓላዊነት” ቀን በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መገኛ ጉባ ወረዳ ማንኩሽ ከተማ ተከብሯል።

ርዕሰ መሥተዳድሩ በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት÷ ውድ ሀብታችን የሆነችው ኢትዮጵያ የጀግኖች መስዋዕትነት ውጤት ናት ብለዋል።

በመስዋዕትነት ሀገርን መጠበቅ ከክብር ሁሉ የላቀ መሆኑን አስገንዝበው÷ ሀገራቸውን ከወራሪ ጠላት በመከላከል ክብሯን የሚጠብቁ ጀግኖች ሁሌም ሊመሠገኑ እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡

አሁንም ተባብረን የሀገራችንን ክብር መጠበቅ ይጠበቅብናል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

የሉዓላዊነት ቀን ኢትዮጵያውያን መስዋዕትነት ከፍለው በማገባደድ ላይ በሚገኙት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መገኛ መከበሩም ልዩ እንደሚያደርገው ተናግረዋል።

በክልሉ በመስዋዕትነት የተገኘውን ሠላም ማጽናት እና ለትውልድ የሚሻገር ብልጽግናን ማረጋገጥ ከሁሉም እንደሚጠበቅም ነው ያስገነዘቡት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.