Fana: At a Speed of Life!

ሉዓላዊነት ሁለንተናዊ መሆን አለበት- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሉዓላዊነት ሁለንተናዊ መሆን አለበት ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሉዓላዊነት ቀንን አስመልክተው በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ሉዓላዊነታችንን ጠብቀን መኖራችን ያኮራናል ብለዋል፡፡

የግዛት ሉዓላዊነት ብቻውን እንደማይቆም ግን ተረድተናል፤ ሉዓላዊነት ሁለንተናዊ መሆን አለበት ነው ያሉት፡፡

የምግብ ሉዓላዊነት፣ የቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት ፣ የበጀት ሉዓላዊነት፣ ታላቁን የሀገር ሉዓላዊነት በጽናት የሚያቆሙ መሆናቸውን አስገንዝበዋል፡፡

እነዚህን የሉዓላዊነት ዘርፎች ለማስከበር አዲሱ ዓይነት ዐርበኝነት ያስፈልገናል፤ ይህም የብሔራዊነት ዐርበኝነት ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

የብሔራዊነት ዐርበኝነት በተሠማራንበት መስክ ሁሉ  የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ሉዓላዊነት ለማስከበር የጊዜ፣ የዕውቀት ፣ የገንዘብና የጉልበት መሥዋዕትነትን መክፈል ነው፤ ሀገር በልጆቿ ትገነባለች ትጠበቃለችም ብለዋል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.