Fana: At a Speed of Life!

ጳጉሜን 2 የሪፎርም ቀን

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) “ሪፎርም ለላቀ አገልግሎት” በሚል መሪ ሃሳብ ጳጉሜን 2 የሪፎርም ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከበረ ነው፡፡

እንደ ሀገር ያጋጠሙ የፖለቲካ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያው ስብራቶችን ለመጠገንና ሁለንተናዊ ብልፅግናን ባጠረ ጊዜ ለማረጋገጥ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ሰፋፊ የሪፎርም ሥራዎች ተጀምሯል፡፡

ከባለፉ ሥርዓቶች የወረስናቸው የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በአሰራራቸውም ሆነ በአስተሳሰባቸው ውስብስብና ቀርፋፋ በመሆናቸው ለሕዝቡ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ በሚፈለገው ጥራትና ፍጥነት መልስ መስጠት አልቻሉም፡፡

በመሆኑም ችግሩን ከስር መሰረቱ ለመቅረፍ የተለያዩ የሪፎርም እርምጃዎች ተወስዷል፡፡

በአንድ በኩል ተቋማቱ በአደረጃጀታቸው እና አሰራራቸው ተለውጠው ፈጣንና ጥራት ያለው አገልግሎት እንዲሰጡ የሲቪል ሰርቪስ ማሻሸያ ፖሊሲ ፀድቆ ወደ ስራ ገብቷል፡፡

በሚቀጥለው አዲስ ዓመትም የመንግስት ዋና የሪፎርም ትኩረት መስክ ሆነው ይቀጥላሉ፡፡

በሌላ በኩል ተቋማት በአገልግሎት አሰጣጣቸው እንዲዘምኑ ለማድረግና ከንክኪ ለማራቅ የተለያዩ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ኢንሼቲቭ ተጀምሯል፡፡

ከዚህ አንፃር “የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ኢንሼቲቭ” ተቀርፆ ወደ ትግባራ ተሸጋግሯል፡፡ ተስፋ ሰጪ ስኬቶችም ተመዝገበዋል፤ በአዲሱ ዓመትም ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.