Fana: At a Speed of Life!

ጳጉሜን 1 የመሻገር ቀን እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) “የመሻገር ጥሪቶች፤ የአዲስ ብርሃን ወረቶች” በሚል መሪ ሃሳብ ጳጉሜን 1 የመሻገር ቀን እየተከበረ ነው፡፡

ቀኑ ሲከበርም ኢትዮጵያን ለማሻገር በተደረጉ ጥረቶች፣ የተገኙ ስኬቶች እየታሰቡ ነው፡፡

ኢትዮጵያን ለማሻገር ትልቅ አቅም የፈጠሩ ስኬቶች በሁሉም ዘርፎች ቢመዘገቡም በቱሪዝም ዘርፍ የተመዘገቡት ድሎች ለመሻገር ቀን “የመሻገር ምልክቶች” ናቸው።

የመሻገር ቀን ምልክት የሆነው ቱሪዝም በዓመቱ ዘርፉን ወደ እውነተኛ ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞች መቀየር ተችሏል።

 

ተደብቀው የነበሩ አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ወደ ኢኮኖሚያ ጥቅሞች ለመቀየር በገበታ ለሀገር ከተደረገው ሰፊ እንቅስቃሴ በተጨማሪ ነባር መዳረሻዎችን የማደስና ደረጃቸውን የማሳደግ ጥረት የመሻገር ምልክት ሆኗል።

በገበታ ለሀገር ከለሙ አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎች ውስጥ ኮይሻ፣ ወንጪ ደንዲና ጎርጎራ ፕሮጀክቶች ይጠቀሳሉ፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.