Fana: At a Speed of Life!

ክልሎቹ ለበዓል የምርት እጥረት እንዳይገጥም ዝግጅት መደረጉን አስታወቁ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለአዲሱ ዓመት ገበያ የምርት እጥረት እንዳይገጥም ሰፊ ዝግጅት አድርገናል ሲሉ የኦሮሚያ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች አስታውቀዋል፡፡

የሰንበት ገበያዎች ለሁሉም ቀናት እንዲቆዩ ማድረግ ፣ ከአምራች ዩኒየኖችና ኢንዱስትሪዎች ጋር የገበያ ትስስር በመፍጠር ገበያው የተሟላ እንዲሆን ተደርጓል ተብሏል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ክፍሌ ታደለ እንደገለፁት፥ ከ419 ሺህ በላይ ኩንታል አትክልትና ፍራፍሬ፣ ከ111 ሺህ 500 በላይ ኩንታል እህል በአምራች ዩኒየኖችና ሕብረት ስራ ማህበራት ወደ ገብያ ገብቷል፡፡

እንዲሁም ወደ 1ነጥብ 9 ሚሊየን ሊትር ዘይትም በመንግሰት ቀርቧል ነው ያሉት፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ንግድ እና ገበያ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ታደሰ ዋጀቦ በበኩላቸው እንዳሉት፥ ለበዓሉ የሚያስፈልጉ የእህል ፣ የእርድ እና የመሰረታዊ ፍጆታ ምርቶች እጥረት አይኖርም፡፡

ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ማግስት የጀመሩትን የቁጥጥር እና ክትትል ስራ አጠናክረው መቀጠላቸውን የቢሮዎቹ ምክትል ሀላፊዎች ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

በማርታ ጌታቸው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.