Fana: At a Speed of Life!

በክረምት በጎ ፈቃድ የዜጎችን ማህበራዊ ችግሮች የማቃለሉ ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል – አቶ ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል በክረምት በጎ ፈቃድ የዜጎችን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች የማቃለሉ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለፁ።

በሐረሪ ክልል በክረምት በጎ ፈቃድ በክልሉ ተወላጅ ባለ ሃብት የተገነባ የአቅመ ደካማ መኖሪያ ቤት አቶ ኦርዲን በድሪ በተገኙበት ተመርቆ ለተጠቃሚ ተላልፏል።

አቶ ኦርዲን በወቅቱ እንደገለጹት÷ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በክልሉ የዜጎችን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች የማቃለሉ ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በመርሐ ግብሩ በክልሉ በርካታ አቅመ ደካማ ዜጎችን በመኖሪያ ቤት ዕድሳት እና በኢኮኖሚ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አስታውሰዋል፡፡

ባለሃብቱ በክልሉ በበርካታ የማህበረሰብን ተጠቃሚነት በሚያረጋግጡ የልማት ሥራዎች እየተሳተፈ እንደሚገኝ መናገራቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ሁሉም ሲተባበር ችግሮችን መሻገር እንደሚቻል የጠቆሙት ርዕሰ መስተዳድሩ÷ አቅም ያላቸው በኢኮኖሚ ደከም ያሉ ዜጎችን በመደገፍ የበኩላቸውን ማህበራዊ ሃላፊነት እንዲወጡ ጠይቀዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.