ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቻይና-አፍሪካ ጉባኤ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓትን ተካፈሉ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቻይና-አፍሪካ ጉባዔ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓትን ተካፍለዋል።
በሥነ-ሥርዓቱ ቻይና ከአፍሪካ ጋር ላላት ትብብር አስር ዘርፎችን ይፋ ማድረጓ ተገልጿል።
ከእነዚህ ውስጥም ንግድ፣ ኢንዱስትሪ ፣ ጤና፣ ግብርና፣ መገናኛ አውታሮች ልማት፣ አረንጓዴ ልማት እና ደኅንነት እንደሚገኙ ተጠቁሟል።
የተጠቀሱት መስኮች ኢትዮጵያ ከትብብር ማዕቀፉ እንድትጠቀም የሚያስችሉ መሆናቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ አመልክቷል።