ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ከሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሱዳን ሉዓላዊ ም/ ቤት ፕሬዚዳንት ጀኔራል አብደል ፈታህ አልቡርሃን ጋር ተወያይተዋል፡፡
ከቻይና-አፍሪካ ትብብር ጉባዔ ጎን ለጎን የተደረገው ውይይት መሪዎቹ ባለፈው ሐምሌ ወር ካደረጉት ምክክር የቀጠለ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡
በውይይታቸውም÷ሰፋ ያለ መጠነርዕይ ባላቸው የሁለትዮሽና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ በትኩረት መምከራቸውን ገልጸዋል፡፡