የኢትዮጵያ እና ሊቢያን ግንኙነት በይበልጥ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር ተደረገ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻይና ቤጂንግ እየተካሄደ ከሚገኘው የአፍሪካ-ቻይና የሚኒስትሮች ጉባዔ ጎን ለጎን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከሊቢያው አቻቸው አል ጣሂር አል ቦውር ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይታቸውም የሀገራቱን ግንኙነት በይበልጥ ማጠናከር በሚቻልበት እና በሁለትዮሽ የጋራ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
በዚህም የሀገራቱን የኢኮኖሚ ትብብር በንግድ እንዲሁም ኢንቨስትመንት ለማጎልበት እና በሰላም ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመሥራት በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡