Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማን ስማርት ሲቲ ማድረግ የሚያስችል ስምምነት ተደረገ

 

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)የአዲስ አበባ ከተማ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር መዲናዋን ስማርት ሲቲ ለማድረግ በትብብር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ይሽሩን አለማየሁ(ዶ/ር) እንዳሉት÷ የመዲናዋ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ መዲናዋን ስማርት ሲቲ ለማድረግ የጀመራቸው የቴክኖሎጂና የመሰረተ ልማት ማስፋፊያዎች የሚበረታቱ ናቸው።

ሚኒስቴሩ የቢሮውን ሀብትና የሰው ሃይል በማብቃት፣ የኢንኩቤሽን ማዕከላትን በማልማት፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርን በማፋጠን፣ የስማርት ሲቲ የልምድ ልውውጥ ለማድረግ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።

አካታችና ሀገር በቀል ዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት እየተደረገ ያለውን ጥረት ለማፋጠን መሰረተ ልማትን በማስፋፋት ረገድ በትብብርና በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ጠቁመው ቴክኖሎጂን ማልማት የሚችልና በአግባቡ የሚጠቀም ዜጋን በማፍራትና በዘርፉ የስራ ዕድል በመፍጠር እንደሚገባም ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ ሰለሞን አማረ÷ በከተማዋ የሚገኙ ቢሮዎችን፣ ክፍለ ከተሞችንና ወረዳዎችን በቴክኖሎጂ በማስተሳሰርና የአገልግሎት አሰጣጡን በማዘመን ሌብነትና ብልሹ አሰራርን ማስቀረት የሚያስችል ስራ መሰራቱን ገልፀዋል።

በተጨማሪም የመሬት አስተዳደርን፣ የኮንስትራክሽን፣ የክፍያ ስርዓትንና ሌሎች የቴክኖሎጂና የመሰረተ ልማት ስራዎች ለምተው ወደ ተግባር መግባታቸውን መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ቢሮው ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የሰው ሃይሉን በማብቃትና የቴክኖሎጂ ሽግግር በማድረግ ከተማዋን ስማርት ሲቲ ለማድረግ እንደሚሰራ አስታውቀዋል።
በውድድሩ ተሳታፊ ለነበሩ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ በነገው እለት የዕውቅና እና የሽልማት መርሐግብር የሚደረግ ይሆናል።

በእንዳልካቸው ወዳጄ

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.