Fana: At a Speed of Life!

ለአፈር ማዳበሪያ ግዥ 1 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር ተፈቀደ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ25 ሚሊየን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ግዥ 1 ነጥብ 3 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር በመንግሥት መፈቀዱ ተገለፀ፡፡

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በ2017/18 የምርት ዘመን ለመስኖ እርሻ የሚውል ዳፕ እና ዩሪያ የአፈር ማዳበሪያ ከውጭ ለማጓጓዝ የግዥ ሂደት መጀመሩ ተመላክቷል።

በዚህም በምርት ዘመኑ 25 ሚሊየን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ግዥ ይፈጸማል ነው የተባለው።

ለ25 ሚሊየን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ (13 ሚሊየን ኩንታል ዩሪያ እና 12 ሚሊየን ኩንታል ዳፕ) ግዥ 1 ነጥብ 3 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር በመንግሥት መፈቀዱን ነው የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን መረጃ የሚያመላክተው፡፡

የኮርፖሬሽኑ የሥራ አመራር ቦርድ በሰጠው ውሳኔ መሰረት ለመስኖ እርሻ የሚውል ዳፕ እና ዩሪያ የአፈር ማዳበሪያ ከመስከረም 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለማቅረብ እንቅስቃሴ መጀመሩ ተገልጿል፡፡

ለ2016/17 የምርት ዘመን በ930 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ከውጭ ከተገዛው 20 ሚሊየን ኩንታል ያህል የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ እስከአሁን ከ18 ነጥብ 8 ሚሊየን ኩንታል በላይ ወደ ሀገር ውስጥ ተጓጉዞ በመሠረታዊ የኅብረት ሥራ ማኅበራት አማካኝነት ለአርሶ አደሮች እየቀረበ ነውም ተብሏል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.