ሊቨርፑል ማንቼስተር ዩናይትድን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሊቨርፑል ማንቼስተር ዩናይትድን 3 ለ 0 አሸንፏል፡፡
ምሽት 12ሰዓት በተካሄደው ጨዋታ ሊቨርፑል በሉዊስ ዲያዝ ሁለት ግቦችና በሞ ሳላህ አንድ ግብ ማንቼስተር ዩናይትድን 3 ለ 0 አሸንፏል፡፡
ቀን 9፡30 ኒውካስል ዩናይትድ ከቶተንሃም ባደረጉት ጨዋታ ኒውካስል ዩናይትድ 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡
በተመሳሳይ ሰዓት የተደረገው የቼልሲና ክሪስታል ፓላስ ጨዋታ 1 አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል፡፡