Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በቻይና- አፍሪካ ትብብር ጉባኤ ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስጠበቅ ትሰራለች-አምባሳደር ተፈራ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)ኢትዮጵያ በቻይና -አፍሪካ ትብብር ጉባኤ ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ስራዎችን ትሰራለች ሲሉ በቻይና የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ተፈራ ደርበው ተናገሩ፡፡

አምባሳደር ተፈራ ደርበው ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ÷ ከጉባኤው ጎን ለጎን የኢትዮጵያን ጥቅም የሚያስጠብቁ ስራዎች ይሰራሉ ብለዋል።

ለዚህም ሰነድ ማዘጋጀትን ጨምሮ ሌሎች የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተሰርተዋል ነው ያሉት።

ከጉባኤው ጎን ለጎን የኢትዮጵያ የስራ ሃላፊዎች ቻይናውያን ባለሀብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ነዋያቸውን እንዲያፈሱ የሚያስችል የውይይት መድረክም እንደተዘጋጀ አንስተዋል።

ቻይና እና ኢትዮጵያ በንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ በልማትና ሌሎች ዘርፎችም አብረው ሲሰሩ መቆየታቸውንና ይህንን ለማጎልበት እንደሚሰራም ተናግረዋል።

በዘንድሮው የቻይና -አፍሪካ ጉባኤ ሰላምና ደህንነት፣ ግብርና፣ የጋራ ልማትን ጨምሮ ሌሎች ጉዳዮች እንደሚመከርባቸው ይጠበቃል።

በአፈወርቅ እያዩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.