የቨርቹዋል መረጃ ደህንነትን ማስጠበቅ ሉአላዊነትን ለመጠበቅ የሚሠራውን ሥራ ምሉዕ ያደርገዋል – ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቨርቹዋል መረጃ ደህንነትን ማስጠበቅ የሀገር ሉአላዊነትን ለመጠበቅ የሚሠራውን ሥራ ምሉዕ ያደርገዋል ¬¬ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ በዛሬው ዕለት በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በመገኘት ይፋዊ ቁልፍ መሠረተ ልማትን (PKI) በይፋ አስጀምረናል ብለዋል።
ይህም የሚታመንና ደህንነቱ የተጠበቀ የዲጅታል መረጃ ልውውጥን የሚያፋጥን ይሆናል ሲሉ በመልዕክታቸው ገልጸዋል።