Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን 1 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ያልተጣራ ትርፍ አገኘ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን 1 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ያልተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ።

የመንግስት የልማት ድርጅት የሆነው ኮርፖሬሽኑ በፕሮጀክቶች አፈጻጸም ዙሪያ የውይይት መድረክ እያካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ በ2016 በጀት ዓመት በበርካታ ችግሮች ውስጥ ያለፈ ቢሆንም በፈተና ውስጥ ሆኖ ስኬት ማስመዝገቡን ተገልጿል።

ይህንን ስኬት ማስመዝገቡ በአፍሪካ በቀዳሚነት ከሚጠቀሱ የልማት ድርጅቶች ውስጥ አንዱ እንዲሆን እንዳደረገው የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ዮናስ አያሌው ተናግረዋል።

ኮርፖሬሽኑ ከተለያዩ የግንባታ ስራዎችና ከኮንስትራክሽን ግብዓት አምራች ኢንዱስትሪዎች ከ11 ነጥብ 8 ቢቢሊን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱ ተገልጿል።

በውሃ፣ በትራንስፖርት፣ በህንፃና በቤቶች ኮንስትራክሽን ዘርፍ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ትላልቅ የልማት ፕሮጀክቶችን እየገነባ ይገኛል።

በአሸናፊ ሽብሩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.