በምስራቅ ዕዝ በኤረር ኢባዳ እርሻ ፕሮጀክት የተሰሩ የልማት ስራዎች ተጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገር መከላከያ ሰራዊት ምስራቅ ዕዝ በኤረር ኢባዳ እርሻ ፕሮጀክት አማካኝነት የተሰሩ የልማት ስራዎች ተጎበኙ፡፡
በጉብኝቱ የምስራቅ ዕዝ ምክትል አዛዥ ሜጀር ጀነራል ፍቃዱ ፀጋዬ፣ ከፍተኛ መኮንኖችን ጨምሮ የምስራቅ ሐረርጌ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
ጉብኝቱ የምስራቅ ዕዝ 47ኛ ዓመት ምስረታ በዓልን አስመልክቶ በመከናወን ያለ ነው።
ዕዙ በእርሻ ፕሮጀክቱ 155 ሄክታር በቆሎ፣ 25 ሄክታር ማሽላ እና 40 ሄክታር ሽንኩርት እያለማ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡
ዕዙ በኤረር ኢባዳ እርሻ ፕሮጀክት የተሰሩ የልማት ስራዎች በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ለገበያ መረጋጋት እገዛ እያደረገ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።
በእዮናዳብ አንዱአለም