Fana: At a Speed of Life!

ውዳሴ ዲያግኖስቲክ ማዕከል ነፃ የምርመራ አገልግሎት ሊሰጥ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)ውዳሴ ዲያግኖስቲክ ማዕከል “ጳጉሜን ለጤና” በሚል መርሐ ግብሩ ከጳጉሜን 1 እስከ 5 ቀን 2016 ዓ.ም የሚቆይ ነፃ የምርመራ አገልግሎት እንደሚሰጥ አስታውቋል፡፡

ነጻ የህክምና አገልግሎቱ ሲቲ ስካን፣ አልትራሳውንድ፣ ራጅ፣ ኢንዶስኮፒና በማዕከሉ የሚሰጡ ሌሎች የምርመራ አገልግሎቶችን የሚያካትት መሆኑን የማዕከሉ ባለቤትና ዋና ሥራ አስኪያጅ ዳዊት ኃይሉ ተናግረዋል፡፡

በአቅም ውስንነት ምርመራ ለማድረግ ያልቻሉ ወገኖች የነጻ ሕክምናው ተጠቃሚ እንደሚሆኑም መናገራቸውን የማዕከሉ መረጃ ያመላክታል፡፡

የጤና ሚኒስትር ተወካይ ዶክተር አስቻለው ወርቁ በበኩላቸው÷ የጤና ተቋሙ በየጊዜው የሚሰጠው ነፃ የሕክምና አገልግሎት የሚበረታታ መሆኑን ገልፀው ሌሎች የሕክምና ተቋማትም ዓርአያነቱን ሊከተሉ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.