33ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባዔ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 33ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባዔ ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመሯል።
ጉባዔው “ፍትሃዊና ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም” በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡
የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በዚህ ወቅት÷በትምህርት ዘርፍ የሚደረገው የማሻሻያ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።
ማሻሻያውን ስኬታማ ለማድረግም ለትምህር ዘርፉ ቁልፍ በሆኑ ጉዳዮች ላይ መሥራት እንደሚገባ ነው የተናገሩት፡፡
ለዘርፉ ስኬት በአራት መሠረታዊ ጉዳዮች ማለትም በጥራት፣ ፍትሃዊነት፣ ሃላፊነት የሚሰማው ትውልድ ማፍራት እና ቅንጅታዊ አሠራር ማጎልበት ላይ በትኩረት መሥራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
በመድረኩ የ2016 ዓ.ም ትምህርት ዘርፍ አፈጻጸም፣ የ2017 ዓ.ም ዕቅድ ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎችና የትምህርት ዘርፉ ሪፎርም ላይ ውይይት እንደሚካሄድ ተመላክቷል፡፡