አትሌት ሲምቦ ዓለማየሁ በሴቶች 3 ሺህ ሜትር መሰናክል ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ አስገኘች
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፔሩ ሊማ እየተካሄደ በሚገኘው ከ20 ዓመት በታች የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አትሌት ሲምቦ ዓለማየሁ በሴቶች 3 ሺህ ሜትር መሰናክል ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ አስገኘች።
አትሌት ሲምቦ በ9 ደቂቃ ከ12 ሰከንድ 71 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት የሻምፒዮናውን ክብረወሰን በመስበር ጭምር ነው ማሸነፍ የቻለችው፡፡
በውድድሩ ላይ የተሳተፈቺው አትሌት ፍሬህይወት ገሰሰ በ9 ደቂቃ ከ34 ሰከንድ ከ50 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት አራተኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቅቃለች።