አየር መንገዱ ከ28 ት/ቤቶች ለተወጣጡ ተማሪዎች ልዩ ስልጠና በመስጠት አስመረቀ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች ለተወጣጡ ተማሪዎች በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስና እና ሒሳብ ትምህርቶች ልዩ ስልጠና በመስጠት አስመርቋል።
ስልጠናው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቦይንግ እና ቲንክ ያንግ ኩባንያ ጋር በመተባበር ነው የተሰጠው፡፡
ሰልጣኞቹ ከ28 የተለያዩ የ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የተወጣጡ የ11ኛ ክፍል ተማሪዎች ሲሆኑ÷መርሐ ግብሩ በኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቪርሲቲ በኩል መሰጠቱ ተጠቁሟል፡፡
የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስና እና ሒሳብ ትምህርቶች (ኤስ ቲ ኢ ኤም) የተሰኘው ፕሮግራም አሁን ላይ ለሁለተኛ ጊዜ እንደተሰጠም የአየር መንገዱ መረጃ ያመላክታል፡፡
ስልጠናው የትምህርት ተደራሽነት በበቂ ሁኔታ ባልተሟላባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ወጣቶች ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡