Fana: At a Speed of Life!

የቻይና ባለሃብቶች በስፋት በኢንዱስትሪ ፓርኮች እንዲሠማሩ እየተሠራ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ተጨማሪ የቻይና ባለሃብቶች በኢንዱስትሪ ፓርኮች እና በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጣና በተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች እንዲሠማሩ እየተሠራ መሆኑ ተመላከተ፡፡

የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሰሐ ይታገሱ (ዶ/ር) በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ከሆኑት ተፈራ ደርበው እና የኢኮኖሚ ዘርፍ ምክትል አምባሳደር ደዋኖ ከድር ጋር ተወያይተዋል፡፡

በዚሁ ወቅት የቻይና ኩባንያዎችና ባለሃብቶች በኢንዱስትሪ ፓርኮችና ድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጣና በፋርማሲዩቲካል፣ በጨርቃጨርቅና ጋርመንት እንዲሁም በግብርና ምርቶች ማቀነባበር ዘርፎች መሠማራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ያሉትን የኢንቨስትመንት አማራጮችም ማስተዋወቅ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.