ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉር የዓለም የጤና ድርጅት መድረክ ላይ እየተሳተፈች ነው
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ የተመራ ልዑክ በአፍሪካ አህጉር የዓለም ጤና ድርጅት መድረክ ላይ እየተሳተፈ ነው።
74ኛው የአፍሪካ አህጉር የዓለም የጤና ድርጅት መድረክ የኮንጎ ብራዛቪል ፕሬዚዳንት ዴኒስ ሳሶ ንጉዌሶ በተገኙበት ዛሬ በብራዛቪልከተማ በይፋ ተጀምሯል፡፡
መድረኩ እስከ ነሐሴ 25 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚካሄድ መገለጹን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
በመድረኩ ክልላዊና አሀጉራዊ የማህበረሰብ ጤና አሁናዊና ቀጣይ ስትራቴጅክ ጉዳዮች ከዓለም ህብረተሰብ ጤና አንፃር ያሉበት አጠቃላይ ሁኔታ ቀርቦ ምክክር እንደሚደረግ ተጠቁሟል፡፡
ላለፉት 10 ዓመታት የአፍሪካ አህጉር የዓለም የጤና ድርጅት ዳይሬክተር ሆነው ያገለገሉት ዶ/ር ማቲሽዲሶ ሞኤቲን የሚተካ አመራር እንደሚመረጥም ተጠቅሷል፡፡