Fana: At a Speed of Life!

በኮሪደር ልማት ሥራ የተመዘገበው ውጤት በተሻለ ፍጥነት ተጠናክሮ ይቀጥላል- አቶ ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል በኮሪደር ልማት ሥራ የተመዘገቡ ውጤቶች በተሻለ ፍጥነት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ርብርብ እንደሚደረግ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለፁ።

አቶ ኦርዲን በድሪ የሐረር ከተማን ስትራቴጂክ የልማት እቅድ ለመምራት ከተቋቋመው ግብረ ሃይል ጋር እየተከናወኑ በሚገኙ የልማት ሥራዎች ላይ መክረዋል።

አቶ ኦርዲን በዚህ ወቅት እንዳሉት÷በክልሉ ገቢራዊ እየሆነ ያለው የኮሪደር ልማት ሥራ የከተማዋን ገፅታ ከመቀየር ባለፈ ምቹ የእግረኛ መንገዶች እንዲኖሩ እያስቻለ ነው።

በተለይ በከተማ ውበት እና ፅዳት የተሰራው ሥራ ከተማዋን ለኑሮና ሥራ የተመቸች በማድረግ ረገድ አበረታች ውጤት ማስገኘቱን ተናግረዋል።

ከተማዋን በፕላንና ስርዓት የምትመራ ለማድረግ ትኩረት መሰጠቱን ጠቁመው÷የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን መንከባከብ እና መጠበቅ ይገባል ብለዋል።

በተለይ ጅምር የልማት ሥራዎችን በጊዜ የለኝም መንፈስ በፍጥነትና ጥራት በማከናወን የማህበረሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ርብርብ እንደሚደረግ ገልፀዋል።

የመንገድ ዳር ንግድን ሥርዓት ከማስያዝ አንፃር የተጀመሩ ሥራዎችን ለማስቀጠል በቁርጠኝነት እንደሚሰራ መጥቀሳቸውንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.