50 ሚሊየን ሊትር የምግብ ዘይት ወደሀገር ውስጥ እየተጓጓዘ ነው
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 50 ሚሊየን ሊትር የምግብ ዘይት ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ እየተጓጓዘ መሆኑ ተገለጸ፡፡
ከጅቡቲ ወደ ተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች እየተጓጓዘ ያለው የምግብ ዘይት የኑሮ ውድነትን ለማሻሻል እና ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል የገበያ ዋጋን ለማረጋጋት ታስቦ በመንግሥት የተገዛ መሆኑን በጅቡቲ የኢትዮያ ኤምባሲ መረጃ አመላክቷል፡፡
በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ፣ የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽንና የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት ከኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር ጋር በመቀናጀት ነው ዘይቱ ወደ ሀገር ውስጥ እየተጓጓዘ የሚገኘው፡፡