የህብረት ስራ ዩኒየኖቹ ከ200 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የትራክተር ግዥ ፈጸሙ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን የሚገኙ ለአራት የህብረት ስራ ዩኒየኖች ከ200 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የ20 ትራክተሮች ግዥ መፈጸማቸው ተገለጸ፡፡
ትራክተሮቹ የተገዙት በህብረት ስራ ማህበር ዩኒየን አርሶ አደሮች በቆጠቡት ቁጠባ መሆኑ ተገልጿል።
በኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪ አዲሱ አረጋ÷ የግብርና ዘርፍን ለመደገፍ መካናይዜሽን ወሳኝ ነው ብለዋል።
በተያዘው የ2017 በጀት ዓመት በርካታ ትራክተሮች የግብርና ዘርፉን ለማሳደግ ወደ ሀገር ውስጥ እንደሚገቡ ጠቁመዋል።
የምስራቅ ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አባቡ ዋቆ በበኩላቸው÷ ግብርናን ለማሳደግ ኋላቀር አሰራሮችን በመተው ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በቤዛዊት ከበደ እና ሙሉጌታ ግርማ