Fana: At a Speed of Life!

በሰሜን ጎንደር በመሬት መንሸራተት የ10 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ አብና ቀበሌ ልዩ ስሙ ኖላ በተባለ ቦታ በመሬት መንሸራተት አደጋ የ10 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ ስምንት ሰዎች ከባድ የአካል ጉዳት ደረሰባቸው፡፡

የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች በደጃች ሜዳ ጤና ጣቢያ የሕክምና እርዳታ እያገኙ መሆኑን የወረዳው የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ተስፋዬ ወርቅነህ ተናግረዋል፡፡

በአደጋው ምክንያት 480 አባወራዎች እና 2 ሺህ 400 የቤተሰብ አባላት መፈናቀላቸውን በመጥቀስ በጊዜያዊ መጠለያዎች እንደሚገኙ ለአሚኮ ገልጸዋል፡፡

ከ35 በላይ የቤት እንሰሳት መሞታቸውን እና ከ30 ሔክታር በላይ በሰብል የተሸፈነ መሬትም ከጥቅም ውጭ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.