Fana: At a Speed of Life!

ክልሉ ሰላም የተረጋገጠበትና የልማት ማዕከል ሆኖ እንዲቀጥል በትኩረት ይሰራል – ወ/ሮ አለሚቱ ኡሙድ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋምቤላ ክልል ሰላሙ የተረጋገጠበትና የልማት ማዕከል ሆኖ እንዲቀጥል መንግስት በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አለሚቱ ኡሞድ ገለፁ።

የጋምቤላ ክልልን እንዲያስተዳድሩ የተመረጡትን አዲሶቹን አመራሮች የሚደግፍ ሰልፍ ጋምቤላ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ ወረዳዎች ተካሂዷል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አለሚቱ ኡሞድ በጋምቤላ ከተማ በነበረው የድጋፍ ሰልፍ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ፥ ሕዝቡ አዲሶቹን አመራሮች አክብሮና ተቀብሎ ሰላሙን በራሱ በማረጋገጡ ሊመሰገን ይገባል ብለዋል።

ክልሉ ሰላሙ የተረጋገጠበትና የልማት ማዕከል ሆኖ እንዲቀጥል መንግስት አበክሮ እንደሚሰራ ነው የገለጹት፡፡

ባለፉት 6 ዓመታት ለውጡን ተከትሎ በርካታ ፕሮጀክቶች የተሰሩ ቢሆንም ሕዝቡ ተገቢው የልማት ተጠቃሚ መሆን እንዳልቻ አንስተዋል፡፡

ይህን ክፍተት የፈጠረው በአመራሩ ቁርጠኝነት ማነስና በተለያዩ ጊዜያት በተከሰቱ ግጭቶች ሳቢያ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

በቀጣይ የሰላሙ ዘብ መሆን ከቻለ አዲሱ የክልል አመራር የክልሉን ሕዝብ የልማት ጥያቄዎች በሚችለው አቅምና በአመራሩ ቁርጠኛነት ለመመለስ ተዘጋጅቷል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.