Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአሶሳ ከተማ የተገነባውን የዳቦ ፋብሪካ መርቀው ከፈቱ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)በቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት አማካኝነት በአሶሳ ከተማ የተገነባውን የዳቦ ፋብሪካ መርቀው ከፈቱ፡፡

ጠቅላይ ሚኒሰትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው እንዳስታወቁት÷የዳቦ ፋብሪካው በቀን 300 ሺህ ዳቦ የማምረት  አቅም እንዳለው ገልፀዋል፡፡

ቀደም ሲል የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ሁለት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችንም መገንባቱን አስታውሰዋል፡፡

በተጨማሪም ፅህፈት ቤቱ በመላው ኢትዮጵያ ከ30 በላይ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና 12 የዳቦ ማምረቻዎችን መገንባቱንም አንስተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.